የባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናል ተመረቀ

ሰብስክራይብ

የባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናል ተመረቀ

አዲሱ ተርሚናል ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ቀጥሎ በኢትዮጵያ ሁለተኛው ትልቅ ተርሚናል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ንግግሮች

አሮጌው ተርሚናል በነበረው ግጭት ጉዳት ደርሶበት የነበረ ቢሆንም ያንን ችግር ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር የተገነባ ነው።

ባሕር ዳር ከታሪክ እስከ ተፈጥሮ የታደለች፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ የልማትና የዕድገት አርአያ መሆን የምትችል ከተማ ናት።

እየተሠሩ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ መንገዶች፣ ድልድይ፣ የኮሪደር ልማት እና እየተጠናቀቀ ያለው ስታዲየም ለከተማዋ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በቨርቹዋል ችሎቶችን መከታተልና ፍትሕን ማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ መሥራቱ የሚያስደንቅ ነው።

ከሀገሪቱ ከተሞች 7ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የከተማዋ ገቢ ለማሳደግ መሥራት ያስፈልጋል።

ልማትን ዘላቂ ለማድረግ ሰላም ወሳኝ መሆኑን በመግለፅ፣ በአንድነትና በትብብር በመሥራት የከተማዋንና የክልሉን እድገት ማፋጠን ይገባል፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0