ሶማሊያ የመጀመሪያውን የባሕር ጉባኤ በማካሄድ የባሕር አቅሟን ለመጠቀም እየሠራች ነው
20:14 05.08.2026 (የተሻሻለ: 20:24 05.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሶማሊያ የመጀመሪያውን የባሕር ጉባኤ በማካሄድ የባሕር አቅሟን ለመጠቀም እየሠራች ነው
የሶማሊያን የባሕር ክልል ደህንነት ማስጠበቅ የሀገሪቱን የኤኮኖሚ አቅም ለመጠቀም ወሳኝ መሆኑን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ማክሰኞ ዕለት በሞቃዲሾ በተከፈተው የመጀመሪያው የሶማሊያ የባሕር ጉባኤ ላይ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የባሕር ላይ የነዳጅ እና ማዕድን ፍለጋ እንቅስቃሴዎች መቀጠላቸውን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፤ የዳሰሳ ጥናቶቹ አዎንታዊ ውጤት ያስገኛሉ በሚል ተስፋቸውን ገልጸዋል።
የሁለት ቀናት ጉባኤው (ሐምሌ 28 እና 29) የሚከተሉትን ዓላማዎች ሰንቋል፡፡
በመንግሥት ተቋማት፣ በዓለም አቀፍ አጋሮች እና በግል ዘርፉ መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር፣
ለባሕር ደህንነት፣ ለባሕር ትራንስፖርት ፣ ለንግድ እና ለኢንቨስትመንት የጋራ ራዕይን ማጎልበት፣
የሶማሊያን ሰማያዊ (የውሃ ዘርፍ) ኢኮኖሚ ዘላቂ ልማት ማፋጠን።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X