ምዕራባውያን 'የሩሲያን ቋንቋ ለማፈን' የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው - በሞልዶቫ የሩሲያ አምባሳደር
18:05 05.08.2026 (የተሻሻለ: 18:14 05.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ምዕራባውያን 'የሩሲያን ቋንቋ ለማፈን' የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው - በሞልዶቫ የሩሲያ አምባሳደር
ምዕራባውያን ሀገራት የሩሲያን ቋንቋ መማር ለሚፈልጉ ሰዎች ዕድል መስጠት አይፈልጉም፤ ነገር ግን በሌሎች የዓለም ክፍሎች ያለው አዝማሚያ የተለየ ነው ሲሉ ኦሌግ ኦዜሮቭ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"በዓረቡ ዓለም እና በአፍሪካ ተቃራኒ የሆነ አዝማሚያ እያየን ነው። የሩሲያ ቋንቋ ዓለም አቀፍ ቋንቋ መሆኑን ስለሚረዱ፣ ቋንቋውን መማር የሚፈልጉ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን አሉ" ሲሉ ጠቁመዋል።
በተለይም በኦዜሮቭ አቅጣጫ ሰጪነት የሚካሄደው "ሩስኪ ግላጎል" (Russky Glagol) የተሰኘው ዓለም አቀፍ የሥነ-ጽሑፍ ውድድር፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ገጣሚያን፣ የተውኔት ጸሐፊዎች እና ተርጓሚዎች የሩሲያን ቋንቋ እንዲያጎሉ ዕድል ይሰጣል ብለዋል።
ℹ "ግላጎል" የሚለው የውድድሩ ሥም ቀደምት ጥንታዊ በሆነው የስላቪክ አልፋቤት "ግላጎሊቲክ" ውስጥ ያለ ፊደል እንዲሁም የመናገር እና ድምፅን የማሰማት ድርጊትን የሚያመላክት ነው።
ሐምሌ 3 የጀመረው የውድድሩ ተሳትፎ ማማልከቻ በrusglagol.org ድረ-ገጽ በኩል እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ ይቆያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X