ናይጄሪያ የ250,000 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ደሞዝ ጨመረች

ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ የ250,000 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ደሞዝ ጨመረች

ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግበራዊ የሚሆነው አዲሱ የደሞዝ መዋቅር የሚከተሉትን የደሞዝ ጭማሪዎች ያካተተ ነው፡፡

▪ከብርጋዴር ጄነራል እስከ ጄነራል (ከኮሎኔል በላይ ያሉ ማዕረገተኞች) - 30 በመቶ

▪ከኮሎኔል እስከ ዋና ወታደራዊ መኮንን - 50 በመቶ

▪ከመደበኛ ወታደር እስከ ምክትል ሃምሳ አለቃ - 80 በመቶ

ለመከላከያ ሰራዊቱ የሚወጣው ዓመታዊ የደሞዝ ወጪ ከ484 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ወደ 679 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ከፍ ይላል ተብሏል።

  ፕሬዝዳንት ቲኑቡ ሰራዊቱ ሽፍታዎችን፣ እገታዎችን እና የሽብርተኝነት ጥቃቶችን በመታገል ረገድ የሚያሳየውን ጀግንነት እና መስዋዕትነት አድንቀዋል።

"በየቤታችን ሰላማችን ተጠብቆ እንድንኖር የሚረዱን ወንዶች እና ሴቶች የሰራዊቱ አባላት ለሀገራችን በሚሰጡት አገልግሎት ወቅት ድጋፍ እና እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል" ብለዋል።

ቪዲዮው የ 2026 የናይጄሪያ ጦር ቀን አከባበር ላይ የተታዩ የናይጄሪያ ጦር መሳሪያዎችን እና ቁሳቁሶችን ያሳያል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0