ግብርናን ከዕርዳታ ተቀባይነት ወደ ብሔራዊ ኢኮኖሚ ዋስትና መሪነት የመቀየር የፖለቲካ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል - የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ

ሰብስክራይብ

ግብርናን ከዕርዳታ ተቀባይነት ወደ ብሔራዊ ኢኮኖሚ ዋስትና መሪነት የመቀየር የፖለቲካ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል - የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ

 

አፍሪካ በዓለም ላይ ካለው ያልለማ ለም መሬት 60 በመቶ የሚሆነውን ይዛ ሳለ በውጭ ዕርዳታ ላይ ትኩረት ማድረጓ ታሪካዊ ተቃርኖ መሆኑን ዶ/ር ኢፋ ሙለታ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

 

“አኅጉሪቱ ወደ ራስን መቻል መጓዝ አለባት። ኢትዮጵያም እንደ ሀገር የብሔራዊ አቅሞችን እና የሕዝብ አቅምን በማንቀሳቀስ የምግብ አቅርቦት ፈተናዎችን በራሷ ሀብት መፍታት የሚያስችላትን ተግባር ሰርታለች።” ሲሉ የሀገሪቱን የስንዴ ምርት ስኬት ጠቅሰዋል፡፡

 

የአፍሪካ ሀብትና ታሪካዊ ተቃርኖ፦ “በዓለም ላይ ካለው ያልለማ መሬት 60 በመቶው የሚገኘው በአፍሪካ ነው::” ያሉት ዶ/ር ኢፋ የአፍሪካውያን ትኩረት ወደ ውጭ እርዳታ መሆኑ ታሪካዊ ተቃርኖም እንስተው “ይህ ደግሞ መለወጥ አለበት” ብለዋል። 

 

የአስተሳሰብና የፖሊሲ ለውጥ አስፈላጊነት፦ የእርዳታ ጥገኝነት አዙሪትን ለመስበር ጠንካራ የፖለቲካ ፍላጎት፣ የፖሊሲ ማሻሻያ እና የአስተሳሰብ ለውጥ የሚያስፈልግ መሆኑን አሳስበዋል።

 

የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ተሞክሮ፦ የሀገር ውስጥ አቅምን በማንቀሳቀስ የምግብ አቅርቦት ፈተናዎችን በራስ ሀብት መፍታት እንደሚቻል በስንዴ ምርት ራስን በመቻል የተረጋገጠ መሆኑን ጠቅሰዋል።

 

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0