ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል አጠቃቀም የሕግ እና የቁጥጥር ማዕቀፎቿን እያጠናከረች ነው - የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን
15:39 05.08.2026 (የተሻሻለ: 15:44 05.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል አጠቃቀም የሕግ እና የቁጥጥር ማዕቀፎቿን እያጠናከረች ነው - የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን
ባለሥልጣኑ፣ የኒውክሌር ኃይልን ለኤሌክትሪክ ማመንጫነት ለመጠቀም ከተያዘው ስትራቴጂካዊ እቅድ ጋር በተጣጣመ መልኩ የኒውክሌር ተቋማትን ቁጥጥር የሚደነግጉ ረቂቅ ደንቦችን ለመገምገም ከመንግሥት ተቋማት፣ ከሙያ ማኅበራት እና ከአጋሮች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
የሰው ኃይል ልማት፣ የሕግ ዝግጅት፣ የፈቃድ አሰጣጥ እና የቁጥጥር አሰራሮች ከዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኃይል ኤጀንሲ መስፈርቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።
ረቂቅ ደንቡ የቦታ መረጣ መስፈርቶችን፣ የአካባቢ እና የሕዝብ ደህንነት ጥበቃን፣ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች መከላከያዎችን እና የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ፕሮቶኮሎችን ያካተተ ነው።
ኢትዮጵያ ከሩሲያው “ሮስቴክናድዞር” እና ከአሜሪካ የኒውክሌር ቁጥጥር ኮሚሽንጋር በአቅም ግንባታ እና በቴክኒክ ዘርፍ በትብብር እየሠራች ይገኛል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X