ቱርክ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ታሪካዊውን አል-ነጃሺ መስጂድ ዕድሳት አጠናቀቀች

© telegram sputnik_ethiopiaቱርክ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ታሪካዊውን አል-ነጃሺ መስጂድ ዕድሳት አጠናቀቀች
ቱርክ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ታሪካዊውን አል-ነጃሺ መስጂድ ዕድሳት አጠናቀቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.08.2026
ሰብስክራይብ

ቱርክ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ታሪካዊውን አል-ነጃሺ መስጂድ ዕድሳት አጠናቀቀች

 የቱርክ ዓለም አቀፍ ትብብር እና ቅንጅት ኤጀንሲ (ቲካ) በኢትዮጵያ፣ ትግራይ ክልል የሚገኘውን ታሪካዊውን አል-ነጃሺ መስጂድ እና በቅጥሩ የሚገኙ መቃብራት ዕድሳት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

የቱርክ ኤጀንሲ በመግለጫው እንዳመላከተው ፕሮጀክቱ፦

የጋራ ባህላዊ እሴቶችን ለማስፋፋት እና የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ተከናውኗል፡፡

ወደ መስጂዱ የሚያመራውን እና "የሶሃባዎች መንገድ" የሚባለውን የእግር መንገድ ማሻሻያ አካቷል።

ታሪካዊ ስፍራውን ለጎብኚዎች ምቹ ያደርጋል፡፡

አካባቢውን የሆቴል፣ የንግድ እና የሙዚየም መሠረተ ልማቶችን በማሳደግ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ያጠናክራል።

ውቅሮ አቅራቢያ የሚገኘው አል-ነጃሺ መስጂድ፣ በአፍሪካ የመጀመሪያው መስጂድ እንደሆነ ይነገራል፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0