ሰቆቃው ሲታወስ፦የሊባኖስ መዲና ቤሩት ከስድስት ዓመታት በፊት የኒውክሌር ያልሆኑ በታሪክ ትላልቆቹን ፍንዳታዎች አስተናግዳለች
16:15 04.08.2026 (የተሻሻለ: 16:24 04.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሰቆቃው ሲታወስ፦የሊባኖስ መዲና ቤሩት ከስድስት ዓመታት በፊት የኒውክሌር ያልሆኑ በታሪክ ትላልቆቹን ፍንዳታዎች አስተናግዳለች
ፍንዳታው እ.ኤ.አ. ነሐሴ 4 ቀን 2020 የቤሩት ወደብን ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን፣ በከተማዋ ትላልቅ ክፍሎች ላይም ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።
የፍንዳታው መንስኤዎች፦
• በዕቃ ማከማቻ መጋዘን ውስጥ የተቀሰቀሰ እሳት፤
• በስፍራው ተከማችቶ የነበረው 2,750 ቶን አሞኒየም ናይትሬት መንደድ፤
• አደገኛ የሆነ ቁሳቁስ አስፈላጊው የደህንነት ጥንቃቄ ሳይደረግበት ለዓመታት ተከማችቶ መቆየቱ።
የጉዳት መጠን እና ድህረ-ውድመት፦
• የሞቱ፦ ከ220 በላይ ሰዎች፤
• የቆሰሉ፦ ከ7,000 በላይ ሰዎች፤
• ተፈናቃዮች፦ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች በመውደማቸው ምክንያት ወደ 300,000 የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡
• የኢኮኖሚ ኪሳራ፦ በ10 ቢሊዮን እና 15 ቢሊዮን ዶላር መካከል ይገመታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X