በኢትዮጵያ በሴቶች የሚመሩ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን ለማቅረብ የሩዋንዳን ገበያ ሊቀላቀሉ ነው
14:25 04.08.2026 (የተሻሻለ: 14:34 04.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ በሴቶች የሚመሩ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን ለማቅረብ የሩዋንዳን ገበያ ሊቀላቀሉ ነው
በሴቶች ባለቤትነት የተያዙ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ማዕቀፍ አማካኝነት ምርቶቻቸውን ወደ ሩዋንዳ ገበያ ለማስገባት እና የቀጣናውን የንግድ ትስስር ለማስፋፋት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገልጿል፡፡
የሴቶች ፈጣን የኢኮኖሚ አቅም ማጎልበቻ ማዕከል (ካዌ) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ንግሥት ኃይሌ ከሩዋንዳ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አንቷን ካጃንግዌ ጋር ተገናኝተው በሴቶች የሚመሩ ኩባንያዎችን የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
በዚህም መሠረት፦
የመጀመሪያውን ይፋዊ የምርት ጭነት በመጪው መስከረም ወር 2019 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ወደ ኪጋሊ ይላካል፡፡
በግብርና ማቀባበር፣ በቆዳ ውጤቶች፣ በጨርቃጨርቅ እንዲሁም በከበሩ ድንጋዮች እና ጌጣጌጥ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ይሳተፋሉ፡፡
ይህ እርምጃ የሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ከቀጣናዊ ገበያዎች ጋር ማገናኘት፣ የሀገራቱን የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥ ማጠናከር እና በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና የሚፈጠሩ የንግድ ዕድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም ያለመ ነው ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X