የአፍሪካ ወጣቶች ለአኀጉሪቱ የሚስማማ የዲሞክራሲ ስርዓት ሞዴል መጠየቃቸውን ጥናት አመላከተ
19:59 03.08.2026 (የተሻሻለ: 20:04 03.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ወጣቶች ለአኀጉሪቱ የሚስማማ የዲሞክራሲ ስርዓት ሞዴል መጠየቃቸውን ጥናት አመላከተ
በ16 ሀገራት የሚገኙ 4 ሺህ 900 በላይ ከ18-24 ዓመት ዕድሜ ባላቸው ወጣቶች ላይ የተካሄደው የ2026 የአፍሪካ ወጣቶች ጥናት እንደሚያመለክተው፤ 73% ያህሉ ዲሞክራሲ የተሻለው የመንግሥት አስተዳደር ሥርዓት እንደሆነ ቢያምኑም፤ 56% የሚሆኑት ግን የምዕራባውያን ዓይነት ዲሞክራሲ ለአፍሪካ አይሆንም ብለዋል።
የጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶች፦
76% የሚሆኑት መሪዎቻቸው የወጣቱን ፍላጎት ያውቃሉ ብለው እንደማያምኑ እና የመንግሥት ሥልጣን ላይ ያሉ ወጣቶች ጥቂት መሆናቸውን ገልጸዋል።
80% የሚሆኑት የጥናቱ ተካፉዮች ወጣት ዕጩዎችን ለሚያቀርቡ ፓርቲዎች ድምፅ የመስጠት ዕድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን በተመሳሳይ 80% የሚሆኑት ደግሞ የተወሰነ የወጣቶች ሚኒስትር እንዲኖር ይደግፋሉ።
65% የሚሆኑት በፕሬዝዳንቶች እና በጠቅላይ ሚኒስትሮች ላይ የዕድሜ ገደብ እንዲጣል የሚደግፉ ሲሆን 57 ዓመት የዕድሜ ጣሪያ እንዲሆን ጠቁመዋል።
የጥናቱ መሥራች አይቮር ኢቺኮቪትዝ፤ "የአፍሪካ ጄን-ዚ ስለሚሉት እውነቱን እንነጋገር፤ እነሱ ዲሞክራሲን አልተዉም። የተዉት ለውጥ ማምጣት በማይችሉ መሪዎችና ተቋማት ስለ ዲሞክራሲ መሰበካቸውን ነው" ብለዋል።
43% የሚሆኑት ምላሽ ሰጪዎች የኢኮኖሚ ጫናዎች ቢኖሩም፤ አፍሪካ በትክክለኛው መንገድ ላይ እየተጓዘች እንደሆነ ያምናሉ። ይህም እ.ኤ.አ በ2024 ከነበረው 37% ጭማሪ ማሳየቱን ያመለክታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X