በሱዳን ሰሜን ዳርፉር ፍርድ ቤት ላይ በተሰነዘረ የድሮን ጥቃት የጎሳ መሪዎችን ጨምሮ ቢያንስ 37 ሰዎች ተገደሉ
20:03 03.08.2026 (የተሻሻለ: 20:04 03.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በሱዳን ሰሜን ዳርፉር ፍርድ ቤት ላይ በተሰነዘረ የድሮን ጥቃት የጎሳ መሪዎችን ጨምሮ ቢያንስ 37 ሰዎች ተገደሉ
በካብካቢያ ጉራ-ዛዊያ ወረዳ በሚገኘው ፍርድ ቤት የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች ስብሰባ ወቅት በተሰነዘረው ጥቃት 37 ሰዎች ሲገደሉ 40 ያህሉ ደግሞ መቁሰላቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል።
ጥቃቱን የተመለከቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 በጉራ-ዛዊያ ወረዳ የጥቃቱ ዒላማ የሆነው ስብሰባ የሱዳን ጦርን የኮርዶፋን ግስጋሴ ተከትሎ የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ያቀረበውን የቅስቀሳ ጥሪ ውድቅ ያደረጉ የሀገር ሽማግሌዎችን ብቻ የተገኙበት እንደነበር የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
🟠 በሌላ በኩል የአማፂው ፓራሚሊተሪ ቡድን የፖለቲካ ክንፍ የሆነው የ "ታሲስ" ጥምረት ጥቃቱን ያደረሰው የመንግሥት ኃይል ነው ብሏል። የሱዳን ጦር ግን እስካሁን ለዚህ ክስ ምላሽ አልሰጠም።
🟠 ጥቃቱ፤ ካርቱምን ከሰሜን ኮርዶፋን ጋር የሚያገናኘው ቁልፍ የወጪ ንግድ መንገድ ነፃ መውጣቱን ጨምሮ፤ የሱዳን ጦር በምዕራባዊ አካባቢዎች ያስመዘገበውን ስትራቴጂካዊ የበላይነት ተከትሎ የመጣ ነው።
🟠 የሱዳን ጦር የአማፂ ቡድኑን አቅም ለማዳከም በዳርፉር በሚገኙ የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ይዞታዎች ላይ የሚያደርገውን የድሮን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X