ዚምቧቤ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን የ400 ሚሊዮን ዶላር የመሠረተ ልማት ፈንድ ይፋ አደረገች

ሰብስክራይብ

ዚምቧቤ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን የ400 ሚሊዮን ዶላር የመሠረተ ልማት ፈንድ ይፋ አደረገች

መንግሥት ቁልፍ የመንገድ ኮሪደሮችን በወቅቱ ለማጠናቀቅና ለማደስ ከሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚያስችል 'የመሠረተ ልማት ፈንድ' እያቋቋመ እንደሚገኝ የገንዘብ ሚኒስትሩ ምቱሊ ንኩቤ በ2026 የግማሽ ዓመት የበጀት ግምገማ ወቅት አስታውቀዋል።

በፈንዱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ፕሮጀክቶች፦

◾ የሃራሬ-ቤይትብሪጅ መንገድ፦ ቀሪ 33 ኪሎ ሜትር ማጠናቀቅ፣

◾ የሃራሬ-ቺሩንዱ መንገድ፦ ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር ሙሉ በሙሉ ማደስ፣

◾የቡላዋዮ-ቪክቶሪያ ፏፏቴ መንገድ፦ ቱሪዝምና የሀገር ውስጥ የጭነት ትራንስፖርትን ለመደገፍ የደረጃ ማሻሻያ።

የፋይናንስ መዋቅር እና የታዩ መሻሻሎች፦

ከተገቡት የመጀመሪያ ቃል ኪዳኖች ውስጥ 100 ሚሊዮን ዶላሩ ከወዲሁ ተገኝቷል፣

የብድር ገንዘቡ የሚሸፈነው ከዚምቧቤ ብሔራዊ የመንገድ አስተዳደር ገቢ ላይ ብቻ ተለይቶ ነው፣

ይህ ዕቅድ በዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ በትራንስፖርት፣ በኃይል፣ በመስኖ፣ በትምህርት እና በጤና ዘርፎች 442 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ከተደረገ በኋላ የመጣ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0