የዩክሬን ጦር በሩሲያ የመዝናኛ ከተማ ጌሌንድዢክ ላይ በፈፀመው ጥቃት ሦስት ህፃናትን ጨምሮ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ
15:40 03.08.2026 (የተሻሻለ: 15:44 03.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዩክሬን ጦር በሩሲያ የመዝናኛ ከተማ ጌሌንድዢክ ላይ በፈፀመው ጥቃት ሦስት ህፃናትን ጨምሮ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ
"የዛሬው ድርጊት የኪዬቭ አገዛዝ ከወታደራዊ መሠረተ ልማቶች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት በሌላቸው ሲቪሎች ላይ ሆን ብሎ የፈፀመው ጥቃት ነው። በህፃናት ላይ የተፈፀመው ይህ ክፉ እና ሰብዓዊነት የጎደለው የሽብር ጥቃት በምንም መንገድ ተቀባይነት የለውም" ሲሉ የክራስኖዳር ግዛት አስተዳዳሪ ተናግረዋል።
ጥቃቱ በጠዋት በድሮን የተፈፀመ ነው። ከድሮኖቹ አንዱ የእረፍት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ ሲቪሎች በነበሩበት አርኪፖ-ኦሲፖቭካ በሚባል የባሕር ዳርቻ ስፍራ እንዳረፈ የክራስኖዳር ግዛት ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
የጉዳት መጠን
ከ6ቱ ሰዎች ሞት በተጨማሪ 40 ሰዎች መቁሰላቸውን እና 17ቱ ሆስፒታል መግባታቸውን የክልሉ ጤና ሚኒስቴር ዘግቧል።
በሲቪሎች ላይ የተፈፀሙ የቅርብ ጊዜ የዩክሬን ጥቃቶች፦
የዩክሬን ጦር ሰኔ 11 ለዕረፍት ወደ ጌሌንድዢክ ይጓዝ የነበረን የቤላሩስ የህፃናት እግር ኳስ ቡድን የጫነ ባስ በድሮን መትቶ የአንዲት ሴት ህይወት ሲያልፍ፤ 6 ህፃናትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች ቆስለዋል።
ከሰኔ 3 እስከ ሰኔ 10 በብሪያንስክ ክልል የተፈፀሙ የዩክሬን የድሮን ጥቃቶች የሁለት ታዳጊዎችን እና የሦስት የህክምና ባለሙያዎችን ህይወት ጨምሮ የ9 ሰዎችን ህይወት የቀጠፉ ሲሆን 22 ሰዎችን ማቁሰላቸውን የሩሲያ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ግንቦት 14 ሉጋንስክ አቅራቢያ በስታሮቤልስክ መማሪያ ቤትን ኢላማ ባደረገ ጥቃት የ21 ሰዎች ህይወት አልፎ 42 ሰዎች ቆስለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X