በሰኡታ የተከሰተው የስደተኞች ቀውስ "በተደራጀ እንቅስቃሴ እንጂ ድንገት የሆነ አይደለም" - የሞሮኮ ባለሥልጣናት
15:22 03.08.2026 (የተሻሻለ: 15:24 03.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በሰኡታ የተከሰተው የስደተኞች ቀውስ "በተደራጀ እንቅስቃሴ እንጂ ድንገት የሆነ አይደለም" - የሞሮኮ ባለሥልጣናት
ከቀናት በፊት በሰኡታ የተከሰተው የስደተኞች ውጥረት በበይነ-መረብ በተሰራጨ የሐሰት መረጃ እና በሕገ-ወጥ የሰው አስተላላፊ መረቦች አማካኝነት የተቀሰቀሰ መሆኑን የሞሮኮ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ራሺድ አል-ኻልፊ ገልጸዋል።
"የሕግ እና የአስተዳደር መረጃዎችን በተሳሳተ መንገድ በመተርጎም ወደ አውሮፓ በቀላሉ መግባት እንደሚቻል አድርገው የተፈጥሩ ማታለሎችን" መመርመር እንደተጀመረም ጠቁመዋል።
▪ ሚኒስቴሩ 40 ሺህ የድንበር ጥሰት ሙከራዎች መደረጋቸውን ዘግቧል።
▪ በድንበር ጥሰት ሙከራው ወቅት 11 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ አንደኛው ከከፍታ በመውደቅ እንዲሁም አስሩ በውሃ በመስጠም ነው።
▪ የሞሮኮ እና የስፔን ባለሥልጣናት ስለ ተጨማሪ የሞት መረጃዎችን በጋራ በማጣራት ላይ ናቸው። የስፔን ባለሥልጣናት 50 ሺህ ሰዎች መግባታቸውን እና 72 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X