የዩክሬን ኃይሎች የኢራን መርከብን ሆን ብለው እንዳጠቁ የሚያሳዩ ማስረጃዎች አሉ - የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
14:22 03.08.2026 (የተሻሻለ: 14:46 03.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዩክሬን ኃይሎች የኢራን መርከብን ሆን ብለው እንዳጠቁ የሚያሳዩ ማስረጃዎች አሉ - የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
የዩክሬን ባለሥልጣናት በካስፒያን ባሕር በሚገኘው የኢራን መርከብ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ባለማወቅ የተከሰተ ነው ሲሉ ለኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢያሳውቁም፤ ቴህራን ግን ጥቃቱ ሆን ተብሎ እንደተፈጸመ የዘለንስኪን ንግግሮች ጨምሮ ግልጽ ማስረጃዎች አሉ ስትል ተከራክራለች።
እስማኤል ባቃኢ በመግለጫቸው ያነሷቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦
ኢራን የዩክሬንን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ እና መሰል ድርጊቶች ወደፊት እንዳይደገሙ ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ትወስዳለች፣
የዩክሬን ድርጊት በኩርዲስታን ያለውን ደህንነት እና የኢራቅን የሉዓላዊነት መብት የሚያኮስስ በመሆኑ አሳሳቢ ነው፣
ኢራን፤ ለአራት ዓመታት ግጭት ውስጥ ያለ ወገን በኢ-መደበኛ መንገዶች ድጋፍ ለማግኘት ሊሞክር እና በአካባቢው አሳች ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችል አስጠንቅቃለች፤ ጉዳዩን በተመለከተ ከኢራቅ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑንም ገልጻለች፣
የኢራቅ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ቃሲም አል-አራጂ፤ ኢራቅ ውስጥ ለዩክሬን ጥቅም የሚሠሩ መረቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና በአካባቢው ኢላማዎችን እንደደበደቡ ማመናቸውን ቀደም ሲል ገልጸዋል፣
ኢራን በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ደህንነቱ የተጠበቀ የመርከብ ጉዞ ለማረጋገጥ እና ጊዜያዊ መስመር ለመዘርጋት ከኦማን ጋር ውይይት እያደረገች ነው። ቴህራን አሜሪካ የምትፈጽመውን ትንኮሳ እና እገዳ እስከቀጠለች ድረስ በወሽመጡ ያለው ሁኔታ ሳይለወጥ እንደሚቀጥል ገልጻለች።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X