የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የጎረቤትና የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት እየጠቀመ ነው - የውኃ ኢነርጂ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopiaየአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የጎረቤትና የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት እየጠቀመ ነው - የውኃ ኢነርጂ ሚኒስትር
የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የጎረቤትና የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት እየጠቀመ ነው - የውኃ ኢነርጂ ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.08.2026
ሰብስክራይብ

የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የጎረቤትና የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት እየጠቀመ ነው - የውኃ ኢነርጂ ሚኒስትር 

እንደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ያሉ ጎረቤት ሀገራት ኢትዮጵያ ከምታካሄደው የተፋሰስ ጥበቃ ሥራ፤ ከተሻሻለ የወንዝ ፍሰትና ከተገራ የጎርፍ አደጋ ተጠቃሚ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።

"ኢትዮጵያ ዛፎችን የምትተክለው ለራሷ ብቻ አይደለም። ተፋሰሶቻችንን በማደስ የካርቦን ልቀትን እንቀንሳለን፣ የኦክስጅን ምርት እንጨምራለን እንዲሁም በተሻሻለ የውሃ ፍሰት ጎረቤት ሀገራትን እንጠቅማለን።"

🪴 በአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ስር ከተተከሉት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መካከል 30% የሚሆኑት ከፍተኛ ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት በሚያበረክቱት በአባይ፣ በባሮ እና በተከዜ ወንዝ ተፋሰሶች ውስጥ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ሱዳን እና ግብፅ ተጨማሪ ውሃ በማግኘት ተጠቃሚ እየሆኑ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ በተፋሰስ ጥበቃ ላይ የምታደርገው ኢንቨስትመንት ዓለም አቀፍ እውቅና ይገባዋል ብለዋል።

"ኢትዮጵያ እነዚህን ተፋሰሶች ለመጠበቅ መሬት፣ ሀብት፣ ጊዜ እና ጉልበት እያፈሰሰች ነው። ይህም ኢኮኖሚያዊ እሴት ያላቸውን ጥቅሞች የሚያስገኝ በመሆኑ እነዚህ አስተዋጽኦዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባላቸው 'የሥነ-ምህዳር አገልግሎት ክፍያ' ማዕቀፎች ስር በሳይንሳዊ መንገድ ሊገመገሙ ይገባል።"

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0