የሱዳን የደህንነት ምክር ቤት በጦር ግንባር ከተመዘገቡ ስኬቶች ጎን ለጎን የተቀናጁ ወንጀሎችን ለመከላከል አዳዲስ እርምጃዎችን ይፋ አደረገ

ሰብስክራይብ

የሱዳን የደህንነት ምክር ቤት በጦር ግንባር ከተመዘገቡ ስኬቶች ጎን ለጎን የተቀናጁ ወንጀሎችን ለመከላከል አዳዲስ እርምጃዎችን ይፋ አደረገ

በጦር ኃይሎች አዛዥ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን የተመራው ምክር ቤት፤ በቅርቡ በጦር ግንባር የተመዘገቡ ስኬቶችን ያደነቀ ሲሆን አጠቃላይ የደህንነት ሁኔታዎችንም ገምግሟል።

የግምገማው ዐበይት ውጤቶች፦

ምክር ቤቱ ከአደንዛዥ ዕፅ፣ ከሰው፣ ከጦር መሣሪያ እና ከወርቅ ሕገ-ወጥ ዝውውር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚያዩ ልዩ ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም ወስኗል።

የሱዳን ጦር እና አባሪ ኃይሎች አባላት በማዕድን ማውጫ ቦታዎች እንዳይገኙ ክልከላ ያስቀመጠ ሲሆን መመሪያውን ጥሰው የተገኙ የጦር መሣሪያዎች እና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እንዲወረሱ አዟል።

የሱዳን ጦር ካርቱምን ከሰሜን ኮርዶፋን ጋር የሚያገናኘውን ስትራቴጂካዊ የወጪ ንግድ መስመር ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። አል-ቡርሃን ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል አማፅያን ነፃ በወጡ አካባቢዎች የሚገኙ የጦር ግንባር ሠራዊት አባላትን ጎብኝተዋል።

ምክር ቤቱ ሀገራዊ ደህንነትን ለመጠበቅ፣ የሕግ የበላይነትን ለማጠናከር እና ማንኛውንም የደህንነት ስጋት ለመጋፈጥ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0