የአፍሪካ የማዕድን ኢንዱስትሪ የኢንቨስትመንት መነቃቃት እያሳየ ነው ተባለ

የአፍሪካ የማዕድን ኢንዱስትሪ የኢንቨስትመንት መነቃቃት እያሳየ ነው ተባለ
ለሰው ሰራሽ አስተውሎት መሠረተ ልማት ወሳኝ ማዕድን የሆነውን የዓለማችንን የመዳብ ምርት 20% ገደማ የምትሸፍነዋ አኅጉሪቱ፤ በማዕድን ኢንዱስትሪዋ ላይ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍሰት እያስተናገደች ትገኛለች።
ከአፍሪካ ማይኒንግ ዊክ ምንጮች በተገኘው መረጃ መሠረት፤ ዓለም አቀፍ የመዳብ ፍላጎት በዓመት ወደ 50 ሚሊዮን ቶን ያድጋል ተብሎ መጠበቁ፤ ለዋና ዋና የአፍሪካ የመዳብ አምራቾች የበርካታ ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ዕድል ይፈጥርላቸዋል።
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚገኘው የካሞአ-ካኩላ የመዳብ ኮምፕሌክስ፤ ከ 8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት የሳበ ሲሆን በአሁን ወቅት በዓመት ወደ 520,000 ቶን የሚጠጋ መዳብ እያመረተ ይገኛል።
ዛምቢያ ለሚንጎምባ የመዳብ ፕሮጀክት 2.2 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት አግኝታለች። ፕሮጀክቱ በ2031 ማምረት ሲጀምር በዓመት እስከ 300,000 ቶን ምርት ይሰጣል።
ቦትስዋና ለኮማካው የመዳብ ማዕድን ማውጫ 1.85 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ያገኘች ሲሆን ከማስፋፊያ ሥራው በኋላ በዓመት 130,000 ቶን መዳብ ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።
በልማት ደረጃ ላይ እያለ 1 ቢሊዮን ዶላር ገደማ መሳብ የቻለው የናሚቢያው ሃይብ የመዳብ ፕሮጀክት፤ የሀገሪቱ ቀዳሚ የመዳብ ማዕድን ማውጫ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የማምረት አቅሙም በዓመት ከ90,000 እስከ 95,000 ቶን መዳብ እንደሚሆን ይገመታል።
ይህ ኢንቨስትመንት የሥራ ዕድልን በመፍጠር፣ የኢኮኖሚ ዘርፎችን በማስፋት እና የአካባቢ መሠረተ ልማቶችን በማሳደግ የአፍሪካ ሀገራትን በእጅጉ ይጠቅማል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X