ኢትዮጵያ የአፍሪካን የልማት ሽግግር በመምራት ላይ ትገኛለች - የፓን-አፍሪካ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ
17:59 02.08.2026 (የተሻሻለ: 18:04 02.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የአፍሪካን የልማት ሽግግር በመምራት ላይ ትገኛለች - የፓን-አፍሪካ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ
ኢትዮጵያ በከተሞች ልማት፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ለዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንቶች ባላት ዝግጁነት የአኀጉሪቱን የልማት ሽግግር እየመራች መሆኗን በአፍሪካ የውጤት ግምገማ ተመራማሪዎች መረብ ሥራ አስፈፃሚ አሞስ ንጁጉና ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።
አፍሪካ ለወጣቶች ሥራ አጥነት፣ የምግብ ዋስትና እጦት እና የአየር ንብረት ለውጥ ላሉ የጋራ ፈተናዎች በምርምር የተደገፉ ሀገር በቀል መፍትሄዎችን ማመንጨት እንዳለባት ጠቁመዋል።
እንደ ንጁጉና ገለጻ፤ የአፍሪካ ኀብረት አጀንዳ 2063ን ለማሳካት ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን፣ የሰዎችን በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት ማረጋገጥ እና በበቂ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ ፖሊሲ ማውጣት ወሳኝ ነው።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ዓይነት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን እንቅስቃሴ ጨምሮ የኢትዮጵያ ተሞክሮዎች ለአፍሪካ ጠቃሚ ትምህርት እንደሚሰጡም አብራርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X