የዚምቧቤ የበጀት ቁጥጥር ለኢኮኖሚ መረጋጋት መሠረት መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ

© telegram sputnik_ethiopiaየዚምቧቤ የበጀት ቁጥጥር ለኢኮኖሚ መረጋጋት መሠረት መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ
የዚምቧቤ የበጀት ቁጥጥር ለኢኮኖሚ መረጋጋት መሠረት መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.08.2026
ሰብስክራይብ

የዚምቧቤ የበጀት ቁጥጥር ለኢኮኖሚ መረጋጋት መሠረት መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ

የዓመቱ አጋማሽ የበጀት ክለሳ፤ መንግሥት ወጪውን በተፈቀደው ገደብ ውስጥ በማስጠበቅ ከቀደመው ከበጀት ወሰን ማለፍ ልማድ መውጣቱንና የማክሮ ኢኮኖሚውን መረጋጋት እንደሚያሳይ የገንዘብ ሚኒስትሩ ምቱሊ ንኩቤ ተናግረዋል።

ከበጀት ክለሳው የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦

▪ በዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ መንግሥት ሥራ ላይ ያዋለው 4.85 ቢሊዮን ዶላር፤ የዓመታዊ በጀቱን 42.5% ይሸፍናል።

▪ እስከ ሰኔ በነበሩት ስድስት ወራት የነበረው 4.2% አማካይ የዋጋ ንረት ካለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ዝቅተኛው ነው።

▪ ኢኮኖሚው መንግሥት በዓመቱ ለማሳካት ካቀደው የ5% ግምት በላይ በ2026 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በ6.8% አድጓል።

የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ እና የነዳጅ ግብርን ማዘግየት ከ74 ሚሊዮን ዶላር በላይ የገቢ ጉድለት ቢያስከትሉም፤ የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር ግን የተመደበው በጀት በቂ በመሆኑ ተጨማሪ እንደማያስፈልግ አስታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0