የኒጀር ጦር ኃይሎች 66ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በኒያሜ ተከበረ
16:09 02.08.2026 (የተሻሻለ: 16:14 02.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኒጀር ጦር ኃይሎች 66ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በኒያሜ ተከበረ
በበዓሉ ላይ የቀድሞ የሀገሪቱ መሪዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የሀገር ጥበቃ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት እንደተገኙ የኒጀር የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በዓሉ ለተሰዉ ወታደሮች እና ለሽብርተኝነት ሰለባዎች ዘላቂ መታሰቢያ ከመሆኑ ባለፈ፤ ሠራዊቱ ለኒጀር ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ያለውን ቁርጠኝነት እንደገና ያረጋገጠበት ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሳላው ባርሙ ተናግረዋል።
በበዓሉ የተካተቱ መርኃ-ግብሮች፡-
▪ ለተሰዉ ወታደሮች የተደረገ የክብር ሥነ-ሥርዓት፣
▪ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት፤
▪ የሀገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎችን ሥራዎች የሚያሳይ ዐውደ ርዕይ።
የሠራዊቱ የትጥቅና ቁሳቁስ መመሪያ ሁለት ሙሉ በሙሉ በኒጀር የተመረቱ "ካኦሴን" ብረትለበስ ተሽከርካሪ እና "ኢናቴስ" ቀላል ፈጥኖ ደራሽ ተሽከርካሪ አስተዋውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X