የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴና የነዳጅ አጠቃቀም የሚቆጣጠር የዲጂታል ሥርዓት ሥራ ጀመረ
15:56 02.08.2026 (የተሻሻለ: 16:04 02.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴና የነዳጅ አጠቃቀም የሚቆጣጠር የዲጂታል ሥርዓት ሥራ ጀመረ
እስካሁን 139 ተቋማት ሥርዓቱን እንደተቀላቀሉ እና 69 ተቋማት ከ7,000 በላይ የመንግሥት ተሽከርካሪዎችን መረጃ እንዳስገቡ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን አስታውቋል።
በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ሁሉም ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ወደ ሥርዓቱ እንዲገቡ ይጠበቃል ተብሏል።
በሌላ በኩል ተቋሙ በመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት ከ597 ቢሊየን ብር በላይ ግዥ በመፈጸም፤ ለዲጂታል ኢትዮጵያ ሽግግር ገንቢ ሚና እየተጫወተ እንደሆነ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X