ዚምቧቤ የሀገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ እና የገቢ ምርቶችን ለመቀነስ የሚያስችል ባለ 16 ነጥብ ዕቅድ አጸደቀች

ዚምቧቤ የሀገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ እና የገቢ ምርቶችን ለመቀነስ የሚያስችል ባለ 16 ነጥብ ዕቅድ አጸደቀች
ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የዚምቧቤ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኮንፈረንስ ላይ ይፋ የተደረገው ይህ የውሳኔ ማዕቀፍ፤ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማስፋፋት እና የሀገር ውስጥ የእሴት ሰንሰለቶችን ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ እና ንግድ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
ከሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ልማት ጥናትና ምርምር ተቋም ጋር በጋራ የተዘጋጀው ይህ እቅድ፤ ዚምቧቤ በሀገር ውስጥ ሊመረቱ ለሚችሉ ምርቶች በየዓመቱ የምታወጣውን ከ2.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገቢ ምርት ወጪን የመቀነስ ግብም አንግቧል።
የዕቅዱ ዋና ዋና የትኩረት ዘርፎች፦
የወተት ምርት እና ማቀናባበር፣
የሸንኮራ አገዳ ማጣራት፣
የማዳበሪያ ቅልቅል ማዘጋጀት፣
የመድኃኒት እና የሕክምና ቁሳቁሶች ፣
የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ምርት፣
የቆዳ ማቀናበር እና የጫማ ምርት፣
ለእንስሳት መኖ የሚሆኑ የቅባት እህሎች መጭመቅ፣
ማዕድናት ላይ እሴት መጨመር እና የብረታ ብረት ምርት።
ዋና ዋና የተቋማት ማሻሻያዎች፦
የረጅም ጊዜ ካፒታል ለማንቀሳቀስ የሚያስችል የኢንዱስትሪ ልማት ባንክ፣
የግል ዘርፍ የመሠረተ ልማት ፋይናንስን ለመሳብ የሚያስችል አደጋ የመቀነሻ ማዕቀፍ፣
ለአቅምን ግንባታ እና የሥራ እድል ፈጠራ ለሀገር ውስጥ ግዢን ቅድሚያ መስጠት፣
የሀገር ውስጥ ምርምሮችን ወደ ንግድ ለማሸጋገር በዩኒቨርሲቲዎች፣ በምርምር ማዕከላት እና በኢንዱስትሪዎች መካከል ቀጥታ ግንኙነት መፍጠር።
የታዩ ለውጦች እና ግቦች፦
የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት ያለው አስተዋጽኦ እ.ኤ.አ ከ2025 16.8% በ2026 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ወደ 17.1% አድጓል፣
የተመረቱ ምርቶች የወጪ ንግድ ገቢ እ.ኤ.አ ከ2021 175.8 ሚሊዮን ዶላር በ2025 ወደ 584.8 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X