ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ክለብ ተመለሱ
14:04 02.08.2026 (የተሻሻለ: 16:21 02.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ክለብ ተመለሱ
ቢሊየነሩ ከያዝነው የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ሀብታቸው የ19.7% ወይም 1.67 ቢሊየን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን የብሉምበርግ የቢሊየነሮች መለኪያ አመልክቷል።
ሀምሌ 25 ይፋ በሆነው የቅርብ ጊዜ ደረጃ፤ ሼሁ ከዓለም 375ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
የስዊዲኑ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ 'ፕሪም' የአል-አሙዲ ዋና የሀብት ምንጭ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን በሳዑዲ አረቢያ እና በኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት፣ በንብረት፣ በግብርና፣ በኃይል እና በማዕድን ዘርፎች ኢንቨስትመንቶች እንዳሏቸውም የሚታወቅ ነው።
ይህ አዲስ ምዕራፍ ሳዑዲ አረቢያ እ.ኤ.አ በ2017 ባካሄደችው የፀረ-ሙስና ዘመቻ፤ ከበርካታ የሳዑዲ መሳፍነት፣ ሚኒስትሮች እና ታዋቂ ነጋዴዎች ጋር መታሰራቸውን ተከትሎ በሀብታቸው ዙሪያ ከተፈጠረው አሻሚ ሁኔታ ማገገማቸውን ያመላከተ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X