- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የኤደን ባሕረ ሰላጤ፡ የባሕር ወንበዴዎች እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ አስፈላጊነት

የኤደን ባሕረ ሰላጤ፡ የባሕር ወንበዴዎች እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ አስፈላጊነት
ሰብስክራይብ
የዓለም አቀፉ የባህር ላይ ጉዞ ድርጅት በሶማሊያ የባህር ዳርቻ እና በኤደን ሰላጤ ላይ የባህር ላይ ወንበዴዎች ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ "አሳሳቢ ነው" ብሏል።
“ሩሲያ ትራዲሽናል (ባህላዊ) የኢትዮጵያ አጋር ነች ስንል መንግስታት ቢቀያየሩ እንኳን የማይቀያየር ወዳጅነት ነው ያላቸው ማለት ነው። የአድዋን ጦርነት ብናነሳ እንኳን [ከኢትዮጵያ ጋር የቆመች] ብቸኛዋ የአውሮፓ ሀገር ነች አይደለም? [...] ለአፍሪካውያንም እኮ ከሩሲያ የሚቅድም ወዳጅ የለም [...] ዛሬ ሩሲያ የባለብዙ ዋልታ ዓለም ስረዐት ወሳኝ አካል መሆኗ ወደአንድ ወገን አዘንብሎ የነበረውን የአዓለም ግንኙነት ስረዓት ሚዛን ለማስጠበቅ አስችሏል” ሲሉ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት እንዳለ ነጉኔ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የዛሬው ድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላትን የጠበቀ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሠረት በማድረግ በኤደን ሰላጤ ላይ የባህር ላይ ውንብድናን ለመከላከል ልትጫወት የምትችለውን ስልታዊ ሚና እንቃኛለን ። ለዚህም በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እንደለ ንጉሴ እንግዳችን ናቸው።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአማርኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0