የሩሲያ ተመራማሪዎች ከወርቅ የሚበልጥ ዋጋ ያለው አዲስ ማዕድን አገኙ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ ተመራማሪዎች ከወርቅ የሚበልጥ ዋጋ ያለው አዲስ ማዕድን አገኙ
የሩሲያ ተመራማሪዎች ከወርቅ የሚበልጥ ዋጋ ያለው አዲስ ማዕድን አገኙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.08.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ተመራማሪዎች ከወርቅ የሚበልጥ ዋጋ ያለው አዲስ ማዕድን አገኙ

 

"ተመራማሪዎቹ አዲሱን ማዕድን ያገኙት በኮላ ባሕረ-ገብ መሬት በሚገኘው የኪቢኒ ተራራ ክፍል ውስጥ ባለው ኪሮቭስኪ ማዕድን ማውጫ ነው። ማዕድኑም 'ኮላ አሽክሮፍታይን' የሚል ሥያሜ ተሰጥቶታል" ሲሉ የሩሲያ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለስፑትኒክ ገልጸዋል።

 

የማዕድኑ ልዩ መለያዎች፦

▪ በድንጋይ ላይ የሚገኝ የአዲሱ ማዕድን በጣም ስስ ሽፋን በአማካይ በአንድ ሚሊሜትር 145 ዶላር የሚያወጣ ሲሆን ይህም ከወርቅ ዋጋ በእጅጉ ይበልጣል።

▪ ይህም ተራ ውብ ድንጋይ ብቻ ሳይሆን የመሬት ቅርፊት ኬሚካላዊ መዝገብ ነው። ኢትሪየም፣ ሲሊከን፣ ፖታሺየም፣ ሶዲየም እና ሙሉ የሜንደሌቭ ንጥረ ነገሮች ሰንጠረዥ በአንድ ክሪስታል ውስጥ ይዟል።

▪ ኮላ አሽክሮፍታይን በውስጡ ካልሲየም፣ ማንጋኒዝ እና ፍሎሪን በመያዙ የሚለይ ሲሆን የክሪስታል መዋቅሩ በሳይንሱ ዓለም ከሚታወቁት በጣም ውስብስብ የማዕድን መዋቅሮች አንዱ ነው።

የተለመደው አሽክሮፍታይን ሮዝ ቀለም ያለው፣ አንፀባራቂ፣ በቀላሉ የሚሰበር እና እጅግ ድንቅ የሆነ የሲሊኬት ማዕድን ሲሆን መገኛውም ግሪንላንድ፣ ካናዳ እና ጣሊያን ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0