ሩሲያ እና ሞሪታንያ በኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
16:13 01.08.2026 (የተሻሻለ: 16:14 01.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ሞሪታንያ በኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሼትኒኮቭ እና የሞሪታንያ የኢኮኖሚ እና ልማት ሚኒስትር አብደላሂ ሼክ ሲዲያ፤ በበይነ-መረብ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት የመግባቢያ ስምምነቱን መፈራረማቸውን የሞሪታንያ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የስምምነቱ ትኩረት የሁለቱ ወገኖች የጋራ ፍላጎት በሆኑት የዓሣ ሀብት፣ ሥነ-ምድር፣ የመሬት ውስጥ ሀብት አጠቃቀም እና በሌሎች ዘርፎች በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚሆን ሼክ ሲዲያን የጠቅሰው ዘገባ አመልክቷል።
"ግብርና፣ የሥነ-ምድር ፍለጋ፣ የማዕድን ማውጣት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል እና የዓሣ ሀብት በሁለትዮሽ ትብብራችን ውስጥ ተስፋ ሰጪ መስኮች ናቸው" ሲሉ ሬሼትኒኮቭ ተናግረዋል።
ሁለቱ ወገኖች በዓሣ ሀብት ዘርፍ ያላቸው ትብብር ከ50 ዓመታት በላይ የዘለቀና የቆየ የጋራ አጋርነት እንደሆነም ተነስቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X