የቤኒን ፕሬዚዳንት በነፃነት ቀን ዋዜማ ለመከላከያ ሠራዊቱ መስዋዕትነት ክብር ሰጡ

© telegram sputnik_ethiopiaየቤኒን ፕሬዚዳንት በነፃነት ቀን ዋዜማ ለመከላከያ ሠራዊቱ መስዋዕትነት ክብር ሰጡ
የቤኒን ፕሬዚዳንት በነፃነት ቀን ዋዜማ ለመከላከያ ሠራዊቱ መስዋዕትነት ክብር ሰጡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.08.2026
ሰብስክራይብ

የቤኒን ፕሬዚዳንት በነፃነት ቀን ዋዜማ ለመከላከያ ሠራዊቱ መስዋዕትነት ክብር ሰጡ

ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ለሀገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር የቤኒን ጦር ኃይሎች ቁርጠኝነት እና መስዋዕትነት ሲያደንቁ፤ "ያለእነሱ የዚህን ምሽት ሥነ-ሥርዓት በሰላም ማካሄድ ባልቻልን ነበር" ብለዋል።

ዛሬ በኮቶኑ የነፃነት ቀን ወታደራዊ ሰልፍ ይካሄዳል። በሥነ-ሥርዓቱ 36 የወታደሮች ቡድን፣ 47 ተሽከርካሪዎች እና አራት የብሔራዊ ባሕር ኃይል መርከቦች ይሳተፋሉ። በተጨማሪም የናይጄሪያ ወታደራዊ ስብስብ ከቤኒን የጦር ኃይሎች ጋር አብሮ እንዲሳተፍ ተጋብዟል።

የዳሆሜ ሪፐብሊክ ትባል የነበረችው ቤኒን ነፃነቷን የተቀዳጀችው እ.ኤ.አ ነሐሴ 1 ቀን 1960 ነበር። ሀገሪቱ አሁን የምትጠቀምበትን "ቤኒን" የሚለውን ስያሜ ያገኘችው እ.ኤ.አ በ1975 ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0