ማይናማር ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ሂደት ልምድ ለመቅሰም ልዑካኗን እንደምትልክ አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopiaማይናማር ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ሂደት ልምድ ለመቅሰም ልዑካኗን እንደምትልክ አስታወቀች
ማይናማር ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ሂደት ልምድ ለመቅሰም ልዑካኗን እንደምትልክ አስታወቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.08.2026
ሰብስክራይብ

ማይናማር ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ሂደት ልምድ ለመቅሰም ልዑካኗን እንደምትልክ አስታወቀች

​ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሚን ኡንግ ላይንግ በጃፓን በማይናማርና በላኦስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ኢትዮጵያ ለአለመግባባቶችና ግጭቶች ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን አንጥሮ ለማውጣት እያካሄደች የምትገኘውን ብሔራዊ ምክክር አድንቀዋል።

 

ከብሔራዊ ምክክሩ ልምድ ለመቅሰም ራሱን የቻለ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

 

በሌላ በኩል በሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች በማጎሪያዎች እንዲገቡ የተደረጉ ኢትዮጵያውያንን ከተደራጁ የወንጀል ቡድኖች ለማስጣል መንግሥታቸው የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

 

አምባሳደሩ በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኙ የነበሩ 1,308 ኢትዮጵያውያን ከዚህ ቀደም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለተደረገው ድጋፍ ምሥጋናም አቅርበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0