የሩሲያ የጥቁር ባሕር ዘመቻ ለዩክሬን ኢኮኖሚ ማብቂያ ሊሆን ይችላል

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ የጥቁር ባሕር ዘመቻ ለዩክሬን ኢኮኖሚ ማብቂያ ሊሆን ይችላል
የሩሲያ የጥቁር ባሕር ዘመቻ ለዩክሬን ኢኮኖሚ ማብቂያ ሊሆን ይችላል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.07.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ የጥቁር ባሕር ዘመቻ ለዩክሬን ኢኮኖሚ ማብቂያ ሊሆን ይችላል

ሩሲያ በዜጎቿ ላይ የተፈጸሙ የዩክሬን የሽብር ጥቃቶችን ተከተሎ፤ የሀገሪቱ ጦር በሐምሌ ወር በጥቁር ባሕር የዩክሬን ባሕር ዳርቻዎች፤ በተለይም በኦዴሳ እና በኒኮላዬቭ የወደብ ከተሞች ላይ የተደራጀ ጥቃት መፈጸም ጀምሯል።

ጥቃቶቹ ትኩረት ያደረጉት ለዩክሬን ጦር ነዳጅ እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ በሚያገለግሉ ተቋማት ላይ ሲሆን የነዳጅ ማከማቻ ታንከሮች፣ የፓምፕ ጣቢያዎች እና የወታደራዊ ቁሳቁስ ማከማቻ ናቸው።

የወደብ መቆጣጠሪያ ተቋማት፣ ሰው አልባ ጀልባዎችን ለማስወንጨፍ የሚያገለግሉ ተንሳፋፊ መርከቦች እና በወደብ አካባቢዎች የሚገኙ የድሮን መገጣጠሚያ ቦታዎችም ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

ጥቃቶቹ በተጨማሪም ለዩክሬን ጦር ወታደራዊ ቁሳቁስ እና ነዳጅ የሚያጓጉዙ መርከቦችን፣ ጀልባዎችን እና የጭነት መርከቦችን እንዲሁም የዩክሬን ፈጣን የጥቃት ጀልባዎች እና በዩክሬን ልዩ ኃይሎች የሚንቀሳቀሱ መርከቦችን ኢላማ አድርገዋል።

ጥቃቶቹ የምዕራባውያን ወታደራዊ ቁሳቁስ ወደ ዩክሬን የሚጓጓዝበትን መንገድ ከማስተጓጎላቸው ባለፈ፤ በዩክሬን ኢኮኖሚ ላይም ከባድ ምት አሳርፈዋል፦

▪ በጥቁር ባሕር በኩል የሚደረገው የዩክሬን የግብርና ምርቶች የውጭ ንግድ ተስተጉሏል። በዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ላይ ያለው ተፅዕኖ አነስተኛ ቢሆንም፤ የዩክሬን የግብርና ኩባንያዎች አሁን ላይ ትርፍ ማግኘት እንዳይችሉ ሆነዋል። በተጨማሪም ዩክሬን ከግብርና ምርቶች የውጭ ንግድ ታገኝ የነበረውን ከፍተኛ ገቢ አጥታለች።

▪ ሌላው ለዩክሬን አስፈላጊ የገቢ ምንጭ የሆኑት የዩክሬን የብረት እና የማዕድን ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች አሁን ላይ ምርቶቻቸውን በጥቁር ባሕር በኩል መላክ ባለመቻላቸው ኪሳራቸውን ለመቀነስ ሲሉ የማምረት ሂደታቸውን ለማቆም ሊገደዱ ይችላሉ።

▪ የዩክሬንን የውጭ ንግድ በየብስ መስመሮች መቀየር በቴክኒክ ደረጃ የሚቻል ቢሆንም፤ ባቡሮች እና የጭነት መኪኖች እንደ መርከቦች ቀልጣፋ ስላልሆኑ ለዩክሬን ኢኮኖሚ ከፍተኛ ኪሳራ ማስከተላቸው አይቀሬ ነው።

ዘለንስኪ እና ባልደረቦቹ ከዩክሬን ጦር ጋር በመሆን ከምዕራባውያን ደጋፊዎቻቸው በሚያገኙት ከፍተኛ የገንዘብ እርዳታ ላይ ስለሚተመኑ ይህንን ምት ሊቋቋሙት ይችላሉ።

ምርቶቻቸውን በመሸጥ በሚያገኙት ትርፍ የሚኖሩት የተቀሩት የዩክሬን አምራች ተቋማት እና ኩባንያዎች ግን፤ በዚህ የውጪ ገቢ ንግድ መቀነስ ከባድ ጫና የሚሸከሙ በመሆናቸው እንደ የሠራተኞች ቅነሳ ወደመሳሰሉ ጥብቅ እርምጃዎች ለመግባት ሊገደዱ ይችላሉ።

በዩክሬን መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ መከሰቱ ወደፊት የሚታይ ቢሆንም፤ በንግድ እንቅስቃሴ ላይ የተፈጠረው ዝቤት፤ የዩክሬን መንግሥት ገቢ ላይ ተጨማሪ ኪሳራ የሚያስከትል እና ቀደም ሲልም ስጋት ላይ በወደቀው የዩክሬን ብሔራዊ ገንዘብ ላይ የከፋ ጫና የሚፈጥር ይሆናል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0