የሱዳን መሪዎች ከኢጋድ ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ፤ ቀጣናዊ ድርጅቱ በካርቱም ሥራውን እንደገና ጀመረ

© telegram sputnik_ethiopiaየሱዳን መሪዎች ከኢጋድ ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ፤ ቀጣናዊ ድርጅቱ በካርቱም ሥራውን እንደገና ጀመረ
የሱዳን መሪዎች ከኢጋድ ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ፤ ቀጣናዊ ድርጅቱ በካርቱም ሥራውን እንደገና ጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.07.2026
ሰብስክራይብ

የሱዳን መሪዎች ከኢጋድ ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ፤ ቀጣናዊ ድርጅቱ በካርቱም ሥራውን እንደገና ጀመረ

​ የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ካሜል ኢድሪስ፤ የምሥራቅ አፍሪካ በይነ-መንግሥታት የልማት ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት እንደገና መከፈቱን ምክንያት በማድረግ ከኢጋድ ዋና ፀኃፊ ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ውይይት አድርገዋል።

​ጽሕፈት ቤቱ ለሰላም፣ ለመልሶ ግንባታ እና ለአካባቢያዊ ትስስር ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለፁት ዋና ፀኃፊው፤ በኤል ፋሸር እና በሌሎች በጦርነቱ በተጎዱ አካባቢዎች የተፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አውግዘዋል።

 

​“በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ መካከል ስትራቴጂካዊ ድልድይ በመሆኗ፤ የሱዳን ሰላም ለቀጣናው መረጋጋት ብቻ ሳይሆን ከሁሉም በላይ የዚህን ግጭት ከባድ ጫና ለሚሸከሙት ሚሊዮኖች ሱዳናውያን ወሳኝ ነው” ብለዋል።

ሱዳን ለሁለት ዓመታት ከታገደች በኋላ ባለፈው የካቲት ወር ነበር ወደ ኢጋድ አባልነቷ ዳግም የተመለሰችው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0