የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ አገልግሎት ከቀደመው ዓመት 27% ብልጫ ያለው 157.2 ቢሊዮን ብር ገቢ አስገባ
14:39 31.07.2026 (የተሻሻለ: 14:44 31.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ አገልግሎት ከቀደመው ዓመት 27% ብልጫ ያለው 157.2 ቢሊዮን ብር ገቢ አስገባ
ገቢው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 7.04 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ጭነት በማጓጓዝ የተገኘ ነው።
ተቋሙ ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዳጅ ማጓጓዝ የጀመረ ሲሆን ይህም አጠቃላይ ካጓጓዘው ጭነት የ1.7 በመቶ ድርሻ እንደሚይዝ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተናግረዋል።
በአገልግሎቱ አፈጻጸም ዙሪያ ሌሎች ነጥቦች፦
▪ በበጀት ዓመቱ ከተጓጓዘው 2 ሚሊዮን ቶን የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 74 በመቶው በተሽከርካሪ፣ 26 በመቶው ደግሞ በባቡር ትራንስፖርት ለተጠቃሚዎች ደርሷል።
▪ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ምርት ላኪዎች 34 ሺህ ኮንቴይነሮችን ማቅረብ ተችሏል።
▪ ተቋሙ በ2030 የኢትዮጵያን የኮንቴይነር አቅርቦት 100 ሺህ ለማድረስ አልሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X