የጋና መንግሥት ፕሬዚዳንታዊ የሥልጣን ዘመን ወደ 5 ዓመት እንዲራዘም እና ዝቅተኛ የመወዳደሪያ ዕድሜ ወደ 35 ዝቅ እንዲል ወሰነ

© telegram sputnik_ethiopiaየጋና መንግሥት ፕሬዚዳንታዊ የሥልጣን ዘመን ወደ 5 ዓመት እንዲራዘም እና ዝቅተኛ የመወዳደሪያ ዕድሜ ወደ 35 ዝቅ እንዲል ወሰነ
የጋና መንግሥት ፕሬዚዳንታዊ የሥልጣን ዘመን ወደ 5 ዓመት እንዲራዘም እና ዝቅተኛ የመወዳደሪያ ዕድሜ ወደ 35 ዝቅ እንዲል ወሰነ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.07.2026
ሰብስክራይብ

የጋና መንግሥት ፕሬዚዳንታዊ የሥልጣን ዘመን ወደ 5 ዓመት እንዲራዘም እና ዝቅተኛ የመወዳደሪያ ዕድሜ ወደ 35 ዝቅ እንዲል ወሰነ

 

"አሁን ሥራ ላይ ያለው የ40 ዓመት ገደብ ብቁ ዜጎች በዕድሜ ምክንያት ብቻ ለከፍተኛው የሥልጣን መንበር እንዳይወዳደሩ ያለአግባብ ያግዳል" ሲሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የፍትሕ ሚኒስትር ዶሚኒክ አኩሪቲንጋ አዪኔ በመግለጫቸው ገልጸዋል።

ሌሎች ዝርዝሮች፦

▪ የፕሬዚዳንታዊ የሥልጣን ዘመኑ እንዲራዘም የተፈለገበት ዓላማ መንግሥታት ፕሮግራሞቻቸውን ለማስፈጸም በቂ ጊዜ እንዲያገኙ ለማድረግ ነው።

▪ በፕሬዚዳንታዊ የሥልጣን ዘመን ገደብ ዙሪያ የሚዘጋጀው ረቂቅ ሕግ እ.ኤ.አ በ2027 ለሕዝብ ውሳኔ ከመቅረቡ በፊት በርካታ የማጽደቅ ደረጃዎችን ማለፍ ይኖርበታል።

▪ የሕዝብ ውሳኔው የሚያልፈው ከተመዘገቡት መራጮች ቢያንስ 40 በመቶ የሚሆኑት በምርጫው ከተሳተፉ እና ድምፅ ከሰጡት ውስጥ 75 በመቶ የሚሆኑት ለውጡን ካጸደቁት ብቻ ነው።

▪ ሁለት የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ረቂቅ ሕጎችን የሚያዘጋጅ አዲስ ኮሚቴ የሚቋቋም ሲሆን ሥራውም እስከ መጪው ጥቅምት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

▪ መንግሥት በተጨማሪም በምርጫው እና እ.ኤ.አ ጥር 7 በሚካሄደው በዓለ-ሢመት መካከል ሰፋ ያለ ግዜ እንዲኖር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው በጥቅምት ወር የመጨረሻ ሳምንት እንዲካሄድ አጽድቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0