አማራ ክልል ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የወርቅ ምርት አስመዘገበ

© telegram sputnik_ethiopiaአማራ ክልል ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የወርቅ ምርት አስመዘገበ
አማራ ክልል ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የወርቅ ምርት አስመዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.07.2026
ሰብስክራይብ

አማራ ክልል ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የወርቅ ምርት አስመዘገበ

 

ክልሉ በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ 357 ኪ.ግ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ልኳል።

 

የክልሉ የማዕድን ዘርፍ ዕድገቶች፦

 

የማዕድን ፍለጋ፦ 5,148 ቶን የብረት ማዕድን በ10 ካሬ ኪሜ ስፋት ተገኝቷል፣ በተጨማሪም 440 ካሬ ኪ.ሜ ስፋት 2.5 ቢሊየን ቶን ግራናይት እና 1.625 ቢሊየን ቶን ጥቁር ድንጋይ ተገኝቷል፣

የተወሰዱ እርምጃዎች፦ በሕገ-ወጥ ምዝበራ ላይ በተወሰዱ የመውረስና የማስተካከያ እርምጃዎች ከ27 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ተችሏል፣

ሕገ-ወጥ የማዕድን ሥራ፦ ከ133 ሺህ 500 በላይ ሜትር ኪዩብ ሕገ-ወጥ ማዕድን ተይዟል።

 

“አፈጻጸሙ የክልሉን የኢኮኖሚ አቅም ከማሳደግ ባለፈ ለውጭ ምንዛሪ ግኝትና ለፋይናንስ እንቅስቃሴ መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል” ሲሉ የክልሉ አስተዳዳሪ አረጋ ከበደ በክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ተናግረዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0