ኢትዮጵያ የአፍሪካን የጤና ፋይናንስ ለመቅረጽ የተዘረጋውን አኅጉራዊ ተነሳሽነት ተቀበለች
19:15 30.07.2026 (የተሻሻለ: 19:24 30.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የአፍሪካን የጤና ፋይናንስ ለመቅረጽ የተዘረጋውን አኅጉራዊ ተነሳሽነት ተቀበለች
ሀገሪቱ "የአፍሪካን የጤና ፋይናንስ መቀየር" የተሰኘውን የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አኅጉራዊ ተነሳሽነት ቀድመው ከተቀበሉ የመጀመሪያዎቹ አራት ሀገራት አንዷ ሆለች።
የተነሳሽነቱ ቁልፍ ጉዳዮች፦
▪ዓላማ፦ በሀገር ውስጥ ሀብት ማሰባሰብ፣ በፖሊሲ ማሻሻያዎች እና ዘመናዊ የፋይናንስ ዘዴዎችን በመጠቀም በአፍሪካ ሀገራት ዘላቂ እና አስተማማኝ የጤና በጀት ሥርዓትን መገንባት።
▪አበርክቶ፦ በተነሳሽነቱ አማካኝነት ለኢትዮጵያ በጤና ፋይናንስ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ የማክሮ ኢኮኖሚ እና የበጀት ሁኔታዎችን ያካተተ ቴክኒካዊ እና ትንተናዊ ድጋፍ ይደረጋል።
▪አተገባበር፦ የትግበራ ሂደቱን የሚከታተል የጋራ ቴክኒክ ቡድን የሚቋቋም ሲሆን የኢትዮጵያ ተሞክሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በሞዴልነት እንዲያገለግል ይሠራል ተብሏል።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፤ “የጤና ፋይናንስን እንደ ማኀበራዊ ወጪ ብቻ ሳይሆን በሰው ሀብት፣ በምርታማነት እና በኢኮኖሚ እድገት ላይ እንደተደረገ ትልቅ ኢንቨስትመንት ማየት እንደሚገባ” አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X