- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ቀጠናዊ የዋጋ ሰንሰለት፡ አፍሪካ ሀብቷን ውስጣዊ አቅም እንዴት ማጠናከር ትችላለች?

ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ቀጠናዊ የዋጋ ሰንሰለት፡ አፍሪካ ሀብቷን ውስጣዊ አቅም እንዴት ማቆየት ትችላለች?
ሰብስክራይብ
አፍሪካ ለዓለም ገበያ በርካታ ጥሬ ዕቃዎችን የምታቀርብ ቢሆንም፣ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶችም ጥገኛ ናት። አሁን ላይ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሲመሠረት፣ ትኩረቱ ወደ ቀጠናዊ የዋጋ ሰንሰለቶች ግንባታ እና የሎጂስቲክስ አውታሮችን በማጠናከር ሀብቱ በአህጉሪቱ እንዲቆይ ማድረግ ላይ እየተሸጋገረ ይገኛል።

" ሁላችንም እንደምናውቀው የቅኝ ግዛት ዘመን የአቅርቦት ሰንሰለቱን በተመቸ ሁኔታ የቀረጸውና ያስቀጠለው፣ ጥሬ ዕቃዎችን ከአፍሪካ ወደ የተቀረው ዓለም በዋናነት ወደ አውሮፓ ለመውሰድ ነበር።" ሲሉ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሎጅስቲክስ እና ዕሴት ሰንሰለት ትምህርት ክፍል ኃላፊ መሳይ አየለ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ የንግድና የሎጂስቲክስ አውታሮቿን በማቀናጀት ከጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት ወጥታ የራሷን የዋጋ ሰንሰለት እንዴት መዘርጋት እንዳለባት እንቃኛለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0