አፍሪካ ከ1950ዎቹ ወዲህ አይታ በማታውቀው የኤል ኒኞ አደጋ ልትመታ እንደምትችል የአፍሪካ ኅብረት አስጠነቀቀ

ሰብስክራይብ

አፍሪካ ከ1950ዎቹ ወዲህ አይታ በማታውቀው የኤል ኒኞ አደጋ ልትመታ እንደምትችል የአፍሪካ ኅብረት አስጠነቀቀ

ይህ የተባለው የኅብረቱ አስቸኳይ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የአደጋውን ሁኔታ፣ ተጽዕኖ እና እንደ አኅጉር ያለውን ዝግጁነት በተመለከተ፤ “የአፍሪካን ዝግጁነት፣ መቋቋም እና የአየር ንብረት እርምጃዎች ማጠናከር” በሚል መሪ ቃል እያካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ መሆኑን የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ገልጿል።

የኅብረቱ የተደራዳሪዎች ቡድን ሰብሳቢ አንትዊ ቦአሲያኮ አሞአህ ምንም እንኳን መልክዓምድራዊ አቀማመጣቸው ቢለያይም ሁሉም የአኅጉሪቱ አካባቢዎች ለአደጋው ተጋላጭ ናቸው ብለዋል። “ለአስከፊ ድርቅ፣ ለከባድ ጎርፍ፣ ለመሬት መንሸራተትና ለሌሎችም ድንገተኛ አደጋዎችና ወረርሽኞች ጭምር ሊዳረጉ ይችላሉ” ሲሉም አክለዋል።

አደጋው ምናልባትም በዋናው የዝናብና የመኸር ወቅት የሚያጋጥም መሆኑ አሳሳቢ ነው ያሉት የኅብረቱ የአየር ንብረት ጉዳዮች አስተባባሪ ጆሊ ዋሳምቦ፤ በአኅጉሪቱ የምግብ ዋስትና ላይ ከባድ ተጽዕኖን ሊያሳርፍና ብዙዎችን ለሞት፣ ስደትና መፈናቀል ሊዳርግ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በአደጋው ምክንያት በደጋማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከሰኔ እስከ መስከረም ባሉት ወራት ደረቃማ፣ ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ባለው አጭር የዝናብ ወቅት ደግሞ ከተለመደው በላይ ከፍተኛ ዝናብ ሊያጋጥም ይችላል ተብሏል።

በዚህም ምክንያት በምስራቅ ኢትዮጵያ፣ በምስራቅ ኬንያ እና ሶማሊያ ከባድ ድንገተኛ ጎርፍ ሊያጋጥም እንደሚችል ተገምቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0