አፍሪካ የወደፊት እጣ ፈንታዋን በእጇ ማስገባት አለባት - የዓለም አቀፍ የጥቁር ህዝቦች ማዕከል

© telegram sputnik_ethiopiaአፍሪካ የወደፊት እጣ ፈንታዋን በእጇ ማስገባት አለባት - የዓለም አቀፍ የጥቁር ህዝቦች ማዕከል
አፍሪካ የወደፊት እጣ ፈንታዋን በእጇ ማስገባት አለባት - የዓለም አቀፍ የጥቁር ህዝቦች ማዕከል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.07.2026
ሰብስክራይብ

አፍሪካ የወደፊት እጣ ፈንታዋን በእጇ ማስገባት አለባት - የዓለም አቀፍ የጥቁር ህዝቦች ማዕከል

የማዕከሉ ዋና ጸሐፊ ጸጋዬ ጫማ፣ ዕጣ ፈንታችንን መወሰን የፖለቲካ ነፃነትን ብቻ ሳይሆን ምጣኔ ኃብታዊ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ሲሉ የዓለም ሕዝቦች ጉባኤ አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን “የምጣኔ ኃብት መነቃቃት፦ ለፓን አፍሪካኒዝም ወሳኝ የሆነው አድማስ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ትይዩ መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡

 

“እጣ ፈንታን መወሰን ዘላቂ ምጣኔ ኃብታዊ እድገትን እውን ለማድረግ፣ ባህልን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ እና በራስ ማንነት ላይ የተመሠረተ ቴክኖሎጂያዊ እመርታን ለማስመዝገብ ወሳኝ ነው” ብለዋል።

 

ዋና ጸሐፊው አክለውም፣ ንግግር ብቻውን ውጤት ስለማያመጣ አፍሪካውያን የትርክታቸው ባለቤት ለመሆን ተጨባጭ ርምጃዎችን መውሰድ እንደሚገባቸው ማሳሰባቸውን የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0