የሀገር ውስጥ ምርቶችን መሸመት “በቢሊዮን የሚቆጠረውን የሲ.ኤፍ.ኤ ፍራንክ ሀገር ውስጥ ማስቀረት” ማለት ነው – ካሜሩናዊ ጋዜጠኛ
09:01 30.07.2026 (የተሻሻለ: 09:04 30.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሀገር ውስጥ ምርቶችን መሸመት “በቢሊዮን የሚቆጠረውን የሲ.ኤፍ.ኤ ፍራንክ ሀገር ውስጥ ማስቀረት” ማለት ነው – ካሜሩናዊ ጋዜጠኛ
የስንዴ ገቢ ምርትን ለመቀነስ፣ አዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎችን ለመፍጠር እና እያሻቀበ የመጣውን የዳቦ ዋጋ ለመግታት ለሚደረገው ጥረት ያግዝ ዘንድ ካሜሩን፦ ከካሳቫ፣ ከበቆሎ፣ ስኳር ድንች፣ ፕላንቴን (እንደ ሙዝ ያለ አትክልት)፣ ማሽላ እና ሚሌት (የማሽላ አይነት) ካሉ የሀገር ውስጥ ምርቶች ምርቶች ተቀምመው በሚዘጋጁ ዱቄቶች ዳቦ ማገገር የሚችሉ 60 ወጣቶችን በሦስተኛው ዙር አሰልጥና አስመርቃለች። ይህም ሀገሪቱ የስንዴ ጥገኝነቷን እንድትቀንስ ተስፋ ሰጪ አማራጭ ሆኗል።
በዚህ ተነሳሽነት ላይ አስተያየታቸውን ለስፑትኒክ አፍሪካ የሰጡት ኤዲ ጁኒየር አዪሲ እንደገለጹት፤ በተጨማሪም ከመንግሥት የሚከተሉት እርምጃዎች እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡
▪ የቁሳቁስ ድጎማ ማድረግ፣
▪ ከግብር ነፃ ማድረ እና
▪ በመንግሥት ግዥዎች ውስጥ የሀገር ውስጥ ዳቦዎች እንዲካተቱ ማድረግ።
በተጨማሪም፣ ሀገሪቱ “ምትክ ዳቦ” የሚለውን ቃል በመተው በመላው ሀገሪቱ “በካሜሩን የተመረተ” የሚለውን ሥያሜ በስፋት ማስተዋወቅ እንዳለባት አክለዋል።
“ዳቦን በሀገር ውስጥ ዱቄት የመጋገር አቅም በ2026 በ5%፣ በ2027 በ10% እና በ2028 በ15% ማሳደግ በመጀመር” ደረጃ በደረጃ መጨመር እንደሚቻል ምክረ–ሐሳብ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X