የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የትምህርትና የጤና ተቋማት የሶላር ሲስተሞችን በባለቤትነት እንዲያስተዳድር የሚያስችል ጥናት ይፋ ሆነ
19:19 29.07.2026 (የተሻሻለ: 19:24 29.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የትምህርትና የጤና ተቋማት የሶላር ሲስተሞችን በባለቤትነት እንዲያስተዳድር የሚያስችል ጥናት ይፋ ሆነ
በ‘አደሌ’ ፕሮጀክት ስር የተጠና አዲስ ጥናት በጤና፣ በትምህርት እና በሌሎች ማኅበራዊ ተቋማት የተተከሉ ከመደበኛ መስመር ውጪ ያሉ የሶላር ሲስተሞች በጥራት እና በዘላቂነት እንዲያገለግሉ አገልግሎቱ በባለቤትነት እንዲያስተዳድራቸው የመፍትሔ ሀሳብ ቀርቧል።
ጥናቱ ሦስት የአሰራር አማራጮችን ያነጻጸረ መሆኑ ሲገለፅ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በባለቤትነት ይዞ በ‘ኃይል እንደ አገልግሎት’ በሚል ሞዴል የሚያስተዳድርበት አማራጭ የተሻለ ሆኖ ተመርጧል።
ከአጋር ሚኒስቴሮችና ክልሎች ጋር በመተባበር የሠራተኞች ሥልጠና የሚሰጥ ሲሆን፤ አገልግሎቱ ከ1,400 በላይ ሲስተሞች መረጃ በመሰብሰብ ሙሉ በሙሉ የጥገና እና አስተዳደር ኃላፊነቱን ይወስዳል ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X