ታዋቂው የሩሲያ ጠፈርተኛ ኦሌግ ስክሪፖችካ በአዲስ አበባው ዓለም አቀፍ የሕዋ ሳይንስ ውይይት ልምዳቸውን አጋሩ

ሰብስክራይብ

  ታዋቂው የሩሲያ ጠፈርተኛ ኦሌግ ስክሪፖችካ በአዲስ አበባው ዓለም አቀፍ  የሕዋ ሳይንስ ውይይት ልምዳቸውን አጋሩ

“ወሰን የለሽ ሕዋ፦ ዓለምን በትምህርት፣ በሳይንስ እና በሰብዓዊ ትብብር ማስተሳሰር” በሚል መሪ ቃል በመዲናዋ በተካሄደው ውይይት፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ታዋቂው ሩሲያዊ የሕዋ ተጓዥ ኦሌግ ስክሪፖችካ ለተማሪዎች እና ለውይይቱ ተሳታፊዎች የሕዋ ጉዞ እና ሌሎች ሙያዊ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

ና ዋና መረጃዎች፦

🟠 ከሩሲያ፣ ብራዚል፣ ስፔን፣ ቱኒዚያ፣ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያ የተወጣጡ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡

🟠ውይይቱ ኢትዮጵያ እያስተናገደች በምትገኘው የዓለም አቀፍ የሕዝብ ጉባኤ አፍሪካ ማዕቀፍ ውስጥ የተካሄደ ነው፡፡

🟠 በ"ዩኒቲ" የበጎ አድራጎት ፋውንዴሽን አዘጋጅነት የሚመራው "አርት ሮኬት II" የተሰኘው ዓለም አቀፍ ሰብአዊ ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል፡፡

"አርት ሮኬት II" ፕሮጀክት በካንሰር ሕመም የተያዙ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሕፃናት ሕልምና ምስሎችን በእውነተኛ የሕዋ መንኮራኩር ወደ ሕዋ የሚልክ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ መሆኑን የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል።

በስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ የተቀረጸ ቪዲዮ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0