ከ700 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙበት "የዓለም ሕዝቦች ጉባኤ አፍሪካ" በአዲስ አበባ ተጀመረ

ሰብስክራይብ

ከ700 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙበት "የዓለም ሕዝቦች ጉባኤ አፍሪካ" በአዲስ አበባ ተጀመረ

በጉባኤው ላይ ከ54ቱም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት እና ከሌሎች የዓለም ሀገራት የተወጣጡ ከ700 በላይ የተቋማት መሪዎች፣ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች፣ ወጣቶች፣ ምሁራንና ተመራማሪዎች መገኘታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

የጉባኤው ዋና ዋና ትኩረቶች፦

ዘላቂ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ኃብታዊ ትስስሮች መፍጠር፣

አፍሪካ የመሠረተ ልማት ነጻነት፣

ዘላቂ ልማት፣

የምግብ ዋስትና

የመረጃ መረብ ደህንነትን ማረጋገጥ እና

ባሕላዊ እሴቶት ጥበቃ።

"አዲስ ዓለም፡ አፍሪካ የጋራ የወደፊት ዕጣ ፈንታን በመቅረጽ ረገድ" በሚል መሪ ቃል ከሚካሄደው ጉባኤ ጎን ለጎን ከ16 የአፍሪካ አገራት የተወጣጡ አርቲስቶች ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡበት የዘመናዊ ጥበብ ዐውደ ርዕይም ተካቷል።

በስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ የተቀረጸ ቪዲዮ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0