ወደ 20 ገደማ የኢትዮጵያ ወጣት እግር ኳስ ልዑክ ቡድን አባላት በስዊድን መጥፋታቸው ተነገረ
15:13 29.07.2026 (የተሻሻለ: 15:14 29.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ወደ 20 ገደማ የኢትዮጵያ ወጣት እግር ኳስ ልዑክ ቡድን አባላት በስዊድን መጥፋታቸው ተነገረ
በስዊድን ጎተንበርግ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የጎቲያ ካፕ የሕፃናትና ወጣቶች እግር ኳስ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩ 20 ያህል ኢትዮጵያውያን የልዑክ ቡድን አባላት መጥፋታቸው ተዘግቧል።
የጠፉት የቡድን አባላት ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 17 ዓመት የሆኑ ታዳጊ ተጫዋቾች እና አብረዋቸው የነበሩ የቡድኑ አመራሮች መሆናቸውን የስዊድን ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።
በውድድሩ ማጠቃለያ ቀን ቡድኑ ያረፈበት ትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች የኢትዮጵያ ቡድን አባላት ያላሳወቁና ዕቃቸውን ጠቅልለው መሄዳቸውን በመታዘባቸው ለፖሊስ ጥቆማ አድርገዋል።
"የቡድኑ አባላት ወደ ሀገራቸው አለመመለሳቸውን አረጋግጠናል። ይሁን እንጂ ድርጊቱ በገዛ ፈቃዳቸው የተከናወነ እንጂ ከጀርባው የሰው መነገድ ወይም ተመሳሳይ ሕገ-ወጥ ድርጊት ስለመኖሩ የሚያሳይ ምንም ዓይነት አመላካች ነገር የለም።" ሲል የስዊድን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X