ኢትዮጵያ ከፍተኛ በጀት የሚያዋጡ የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራትን ጎራ ተቀላቀለች
13:44 29.07.2026 (የተሻሻለ: 13:54 29.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከፍተኛ በጀት የሚያዋጡ የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራትን ጎራ ተቀላቀለች
ትናንት መካሄድ በጀመረው 49ኛው የሕብረቱ የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ሕብረቱ ከውጭ ጥገኝነት ተላቆ በበጀት ራሱን ሊችል እንደሚገባ ያሳሰቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ኢትዮጵያ የነበረችበትን የመዋጮ ደረጃ በማሻሻል ከፍተኛ በጀት የሚያዋጡና
የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆኑ አባል ሀገራትን ጎራ (Tier One) ለመቀላቀል መወሰኗን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያን ተከትሎ፣ ኬንያ ቀደም ሲል በግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ አልጄሪያ እና ሞሮኮ ብቻ ተይዞ የነበረውን ጎራ ለመቀላቀል ስለመወሰኗም ታውቋል። ይህም የሕብረቱን 45 በመቶ መደበኛ በጀት ይሸፍኑ የነበሩ ሀገራትን ቁጥር ወደ ስምንት አሳድጓል።
የ2026 የሕብረቱ ሊቀመንበር የሆነችው ቡሩንዲ፣ የሕብረቱን የፋይናንስ ነፃነት ለማጠናከር የተነደፈውን የ0.2 በመቶ የገቢ እቃዎች ታሪፍ ለመተግበር ስለመወሰኗም በስብሰባው መክፈቻ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X