የአፍሪካ ሕብረት አምባሳደር ጆሴፋ ሳኮን ለተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ብቸኛ እጩ አድርጎ አቀረበ

© telegram sputnik_ethiopiaየአፍሪካ ሕብረት አምባሳደር ጆሴፋ ሳኮን ለተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ብቸኛ እጩ አድርጎ አቀረበ
የአፍሪካ ሕብረት አምባሳደር ጆሴፋ ሳኮን ለተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ብቸኛ እጩ አድርጎ አቀረበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.07.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ሕብረት አምባሳደር ጆሴፋ ሳኮን ለተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ብቸኛ እጩ አድርጎ አቀረበ

ሕብረቱ የቀድሞ የአግሮ-ኢኮኖሚክስ እና የዘላቂ አካባቢ ጥበቃ ኮሚሽነሩን አምባሳደር ጆሴፋ ሳኮን የፋኦ ብቸኛ እጩ አድርጎ ያቀረበው ትናንት ማካሄድ በጀመረው 49ኛው የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

በጣሊያን የአንጎላ አምባሳደር እና በሮም ለሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ተወካይ የሆኑት አምባሳደር ሳኮ፣ የምግብ ዋስትናን እና ዘላቂ የእርሻ ልማትን ለማሳደግ ያላቸውን ራዕይ ለሕብረቱ የሚኒስትሮች ኮሚቴ አቅርበው አዎንታዊ ምላሽ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

ጆሴፋ የሚመረጡ ከሆነ፣ እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 2019 ጀምሮ የመጀመሪያው ቻይናዊ በመሆን ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት በመመራት ላይ የሚገኙትን ኩ ዶንግዩን የሚተኩና ለቀጣዮቹ 4 ዓመታት የሚያገለግሉ ይሆናል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0