ከ1.32 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያወጡ የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች ፀድቀው ወደ ትግበራ ገብተዋል - የፕላንና ልማት ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

ከ1.32 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያወጡ የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች ፀድቀው ወደ ትግበራ ገብተዋል - የፕላንና ልማት ሚኒስቴር

ሚኒስቴሩ፣ በ2018 በጀት ዓመት የአካባቢና አየር ንብረት ለውጥ ዘርፍ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት፣ መንግሥት የካርቦን ገበያ ስትራቴጂውን እያሰፋ ባለበት ወቅት የአየር ንብረት ፋይናንስ ፕሮጀክቶች 1.32 ቢሊዮን ዶላር መድረሳቸውን አስታውቋል።

ብሔራዊ የካርቦን ገበያ ስትራቴጂ እና አዋጅ የጸደቀ ሲሆን፣ ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የካርቦን ንግድ እንድትሳተፍና የካርቦን ክሬዲት እንድታገኝ የሚያስችል ሕጋዊ ማዕቀፍ መፍጠሩን ጠቅሶ የዘገበው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው።

ኢትዮጵያ 3ኛውን በሀገር ደረጃ የተወሰነ ብሔራዊ አስተዋጽኦ ለተባበሩት መንግሥታት ያቀረበች ሲሆን፣ እስከ እ.ኤ.አ 2035 የሙቀት አምጪ ጋዞች ልቀትን በ70.3% ለመቀነስ እና 106 ቢሊዮን ዶላር የሚያስፈልገውን ዕቅድ ለመተግበር ሥራ መጀመሯ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ለልማት አጋሮች የፋይናንስ ድጋፍ የቀረቡ ተጨማሪ 26 የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች የተዘጋጁ ሲሆን፣ የመረጃ ጥራትን የሚያረጋግጡ ዲጂታል የክትትልና ማረጋገጫ ሥርዓቶችን የመዘርጋት ሥራ እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0