በሰውነቱ ጥይት ይዞ 6 ዓመት የኖረው ወጣት፡- እንዴት ሊተርፍ ቻለ?

ሰብስክራይብ

በሰውነቱ ጥይት ይዞ 6 ዓመት የኖረው ወጣት፡- እንዴት ሊተርፍ ቻለ?

የ20 ዓመቱ መሐመድ ፋይሰል ጃማ በ14 ዓመቱ ከትምህርት ቤት ሲመለስ በድንገት በተተኮሰ ጥይት ከተመታ በኋላ ጥይቷ በትክሻው በኩል ገብታ ከአከርካሪውና ከጎድን አጥንቱ አቅራቢያ ተሰንቅራ ለዓመታት የዘለቀ ከፍተኛ ሕመም፣ ድንዛዜና የጭንቀት ስሜት እየፈጠረችበት ኖሯል፡፡

ወጣቱ በሕንድ ኒው ዴልሂ የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች በተደረገለት የአምስት ሠዓታት ውስብስብ ቀዶ ሕክምናበተሳካ ሁኔታ ጥይቱ ማውጣት መቻሉን የሕንድ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ከስኬታማው የቀዶ ሕክምና በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ታካሚው፣ "ባለፉት ዓመታት ጥይቷን ተሸክሜ ለመኖር ብሞክርም ዘላቂ መፍትሔ እፈልግ ነበር፤ ዛሬ ጥይቷ ወጥታ አዲስ እፎይታና ተስፋ ስላገኘሁ ሕክምና ያደረጉልኝን ሐኪሞች እጅግ አመሰግናለሁ" ሲል ገልጿል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0