የአፍሪካ ሀገራት ድንበር ተሻጋሪ የደህነት ስጋቶች የተቀናጀ ቀጣናዊ እና አኅጉራዊ ምላሽን ይሻሉ – ኢትዮጵያዊ ወታደራዊ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ሀገራት ድንበር ተሻጋሪ የደህነት ስጋቶች የተቀናጀ ቀጣናዊ እና አኅጉራዊ ምላሽን ይሻሉ – ኢትዮጵያዊ ወታደራዊ ባለሙያ

አኅጉሪቱ በአሁኑ ወቅት ባሕላዊ እና አዳዲስ የደህንነት ስጋቶች ተጋርጠውባታል ሲሉ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ የአዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ ምክትል አዛዥ ለስርዓተ ትምህርት ልማት ዶ/ር ደምሌ ሞላው ኢትዮጵያ የአፍሪካ የተጠንቀቅ ኃይል በአስቸኳይ እንዲንቀሳቀስ ያቀረበችውን ጥሪ አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

“ሽብርተኝነት፣ ፅንፈኝነት፣ የርስ በርስ ጦርነቶች፣ ሕገ-መንግሥታዊ ያልሆኑ የመንግሥት ለውጦች፣ የባሕር ላይ ደህንነት ስጋቶች፣ የሳይበር ጥቃቶች እና የተደራጁ ወንጀሎችን ጨምሮ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ችግሮች በተፈጥሯቸው ድንበር ተሻጋሪና ከአንድ ሀገር ወሰን በላይ የሚዘልቁ በመሆናቸው፣ የተቀናጀ ቀጣናዊና አኅጉራዊ ምላሽን ይፈልጋሉ።” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ባለፍው ሳምንት ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 1345ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ፤ የአፍሪካን የደህንነት ሁኔታ ለማጠናከር የአፍሪካ የተጠንቀቅ (ተጠባባቂ) ኃይል ወደ ሥራ እንዲገባ ጥሪ አቅርባለች፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0