"በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ቋሚ መቀመጫ ጉዳይ አሁን ልናስመዘግበው የሚገባን ሌላኛው የዓድዋ ድል ነው" - ኢድዋርዶ ቢዚማና

© telegram sputnik_ethiopia"በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ቋሚ መቀመጫ ጉዳይ አሁን ልናስመዘግበው የሚገባን ሌላኛው የዓድዋ ድል ነው" - ኢድዋርዶ ቢዚማና
በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ቋሚ መቀመጫ ጉዳይ አሁን ልናስመዘግበው የሚገባን ሌላኛው የዓድዋ ድል ነው - ኢድዋርዶ ቢዚማና - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.07.2026
ሰብስክራይብ

"በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ቋሚ መቀመጫ ጉዳይ አሁን ልናስመዘግበው የሚገባን ሌላኛው የዓድዋ ድል ነው" - ኢድዋርዶ ቢዚማና

አፍሪካ የሌለችበት ዓለም አቀፍ አስተዳደር ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ኢድዋርዶ ቢዚማና ተናገሩ።

“አፍሪካ ዛሬ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ውስጥ የማትታለፍ ዋና ተዋናይ መሆኗን እያረጋገጠች ትገኛለች” ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “አፍሪካ የሌለችበት ዓለም አቀፍ አስተዳደር ያልተሟላ በመሆኑ ውጤታማ ሊሆን” እንደማይችል ዛሬ በተከፈተው የምክር ቤቱ 49ኛ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።

የአፍሪካ የቡድን 20 አባልነት አዲ ምዕራፍ ቢሆንም፣ በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ፍትሐዊ እና ቋሚ ውክልና የማግኘት የአኅጉሪቱን ዐቢይ ጥያቄ ሊጋርደው እንደማይችል አጽንኦት ሰጥተውበታል።

የዓለም የአስተዳደር መዋቅር የ21ኛውን ክፍለ ዘመን ነባራዊ ሁኔታ ሊያንጸባርቅ ይገባል ያሉት አምባሳደሩ፣ አፍሪካ የሌለችበት የዓለም አስተዳደር ያልተሟላ በመሆኑ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል አስጠንቅቀዋል።

አፍሪካ ከአሁን በኋላ ከሕግ እና ደንብ ተቀባይነት ተላቅቃ፣ በኩራት እና በቁርጠኝነት የሕግ እና የደንብ አውጭነት ሚናዋን ልትወጣ ይገባል ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ “ልናስመዘግበው የሚገባን ሌላኛው የዓድዋ ድል ይህ ነው” ማለታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0