ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ካውንስል ምድብ 2 ምርጫ የአፍሪካ ዕጩ ሆና በይፋ ተሰየመች
16:49 28.07.2026 (የተሻሻለ: 16:54 28.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ካውንስል ምድብ 2 ምርጫ የአፍሪካ ዕጩ ሆና በይፋ ተሰየመች
የአፍሪካ አባል ሀገራት በአንድ ድምፅ በደረሱበት ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ በሚካሄደው የዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ካውንስል ምድብ 2 ምርጫ አኅጉሪቱን ወክላ እንድትወዳደር በይፋ ተሰይማለች።
ውሳኔው ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ዘርፍ ያላትን አመኔታ፣ ተፅዕኖ እና መሪነት የሚያሳይ ትልቅ ድል ተደርጎ ተወስዷል።
ውክልናው ባለድርሻ አካላትን አሳትፎ በተደረገ ሁሉን አቀፍ ከፍተኛ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ጥረት የተገኘ መሆኑ ተመላክቷል::
ይህ እጩነት ኢትዮጵያ አፍሪካን በዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ካውንስል በብቃት ለመወከል እና በአኅጉሪቱ የአቪዬሽን ልማትና ትብብር ላይ ያላትን ሚና የበለጠ ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል ሲል የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X